የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት
✣ ሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።
የኔ ዓላማ ግእዝን በድኅረ ገጽ በቀጥታ (online through web-site) አስተምሬ ገንዘብ ለማግኘት አይደለም ፤ ግእዝን ለማስፋፋት ካለኝ ቁርጠኛ ፍላጎት እንጂ። ቢሆንም ግን መጠነኛ ክፍያ እንዲኖረው ያሰብኩት በሦስተ ምክንያቶች ነው። እነሱም
፩, ጽሑፋን /ኖቱን/ ለማዘጋጀት ጊዜና ዕውቀት ስለሚጠይቅ ፦
፪, አብዛኛው ሰው ክፍያ ካልከፈለ ስለማይከታተል ፦
፫, የኢንተርኔትና የድኅረ ገጽ ሰርቨር ኪራይ ክፍያ ወጭ ስላለው ነው።
ስለዚህ አሁንም የእናንተን አስተያየት በመቀበል ክፍያውን በዐመት 500 ብር እንዲሆን አድርጌአለሁ።
አስተያየት ካላችሁ ጻፉልኝ እቀበላለሁ።
በተጨማሪም ክፍያ የምትከፍሉት
* በንግድ ባንክ ቁጥር 1000271433232 ሲሆን
(በውጭ ሃገር ለምትገኙና በዚህ ሃገር ክፍያ ማስፈጸም ለማትችሉ SWIFT Address መጠቀም ትችላላችሁ።
ይህም CBETETAA 1000271433232 ነው።)
ገቢ የተደረገበትን የባንክ ደረሰኝ ፎቶ በማንሳት (በሞባይል ባንኪንግ ተጠቅማችሁ ከሆነ ደግም screen shot በማድረግ) 'Upload Image' የሚለውን በመጫን ፎቶውን ያስገቡት ። ቀጥሎም አድራሻዎትንና የተላከበትን ወይም ያስገቡበትን መለያ ቁጥር (transfer reference) ከዚህ በታች ባለው የመረጃ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ያስገቡ።
ከጨረሱ በኋላ የይለፍ ቃል እንዲላክላችሁ በምትፈልጉት የ e-mail አድራሻችሁ ወደ info@lisanegeez.com (click link) በመላክ የይለፍ ቃል (user name and password) የሚላክላችሁን አድራሻ ማሳወቅ ያስፈልጋል። ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ወደዚሁ አድራሻ መልእክት ይላኩ።
ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ
ዋቤ መጻሕፍት
፩, መዝገበ ሰዋስው ወግሰ ወመዝገበ ቃላት ፦ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
፪, ፍኖተ ግእዝ ፦ ያሬድ ፈንታ
፫, መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው መርኆ መጻሕፍት ፦ ያሬድ ሽፈራው
፬, ጥንታዊ ግእዝ በዘመናዊ አቀራርብ ፦ ዜና ማርቆስ
፭, የልሳነ ግእዝ መማሪያ መጽሐፍ ፦ መ/ር ኀይለ ኢየሱስ መንግሥት
፮, መርኆ ሰዋስው ፦ መ/ር ዘርዐ ዳዊት
ስለ ግእዝ
ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....