headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት


➤ ክፍለ ትምህርት መግቢያ ፪

፩. ፯ ደቃልው (ዝርዋን)ፊደላት

➤ የግእዝ ቋንቋ ከዋናዎቹ ፊደላት በተጨማራ ፬ ዝርዋን ፊደላት አሉት።

እነሱም እያንዳንዳቸው ወደ ጎን ፬ ቅጥያዎች አሏቸው። ስለዚህ ዐራት ሲባዛ በአምስት ፳ ይሆናሉ። እነዚህን ፊደላት ብዙ ሰው ለይቶ አያውቃቸውም።

➤ እነዚህ ፊደላት ካዐብና ሳብዕ የላቸውም። በተጨማሪም ከመሥራች ፊደላት ይመሰረታሉ።

➤ መስራች ፊደላት ----- ➤ ዝርዋን ፊደላት

ምሳሌ፦
➙ ገ ----- ➙ ጐ
➙ ኀ ----- ➙ ኈ
➙ ከ ----- ➙ ኰ
➙ ቀ ----- ➙ ቈ

ወደ ጎን አምስት እርከኖች አሏቸው።
እነሱም፦

➙ ጐ ➙ ጒ ➙ ጓ ➙ ጔ ➙ ጕ
➙ ኈ ➙ ኊ ➙ ኋ ➙ ኌ ➙ ኍ
➙ ኰ ➙ ኲ ➙ ኳ ➙ ኴ ➙ ኵ
➙ ቈ ➙ ቊ ➙ ቋ ➙ ቌ ➙ ቍ
ናቸው።

እነዚህ የመጀመሪያው እንደ ግእዝ ፣ ሁለተኛው እንደ ሣልስ ፣ ሦስተኛው እንደ ራብዕ ፣ አራተኛው እንደ ኀምስና አመስተኛው እንደ ሳድስ ድምፅ በመምሰል ይነበባሉ።

፩. ፰ የፊደልና የቁጥር ዝምድና

የግእዝ ፊደልና ቁጥር ሲመሰረቱ ጀምሮ ዝምድና አላቸው።

ለምሳሌ
፮ ቁጥር ከ "ጌ" ፊደል ጋር
፯ ቁጥር ከ "ጊ" ፊደል ጋር
፱ ቁጥር ከ "ሀ" ፊደል ጋር
፳ ቁጥር ከ "ለ" ፊደል ጋር
፵ ቁጥር ከ "ሣ" ፊደል ጋር
፶ ቁጥር ከ "ሃ" ፊደል ጋር
ወዘተ ተመሳስለው የተፈጠሩ ናቸው።

ሌላው ደግሞ ፊደሉ በቁጥር ተቀምሮ የተመሰረተ ነው።

ለምሳሌ፦
➤ ፊደል --- ➤ ቁጥር --- ➤ መጠሪያ
➙ አ --- ➙ ፩ --- ➙ አሐዱ
➙ በ --- ➙ ፪ --- ➙ ክልኤቱ
➙ ገ --- ➙ ፫ --- ➙ ሠለስቱ
➙ ደ --- ➙ ፬ --- ➙ አርባዕቱ
➙ ሀ --- ➙ ፭ --- ➙ ኀምስቱ
➙ ወ --- ➙ ፮ --- ➙ ስድስቱ
➙ ዘ --- ➙ ፯ --- ➙ ሰብዐቱ
➙ ሐ --- ➙ ፰ --- ➙ ስምንቱ
➙ ጠ --- ➙ ፱ --- ➙ ተሰዐቱ
➙ የ --- ➙ ፲ --- ➙ ዐሥርቱ
➙ ከ --- ➙ ፳ --- ➙ እሥራ
➙ ለ --- ➙ ፴ --- ➙ ሠላሳ
➙ መ -- ➙ ፵ --- ➙ አርባዕ
➙ ነ --- ➙ ፶ --- ➙ ሃምሳ
➙ ሠ --- ➙ ፷ --- ➙ ስሳ
➙ ዐ --- ➙ ፸ --- ➙ ሰብዓ
➙ ፈ --- ➙ ፹ --- ➙ ሰማንያ
➙ ጸ --- ➙ ፺ --- ➙ ተስዓ
➙ ቀ --- ➙ ፻ --- ➙ ምእት
➙ ረ --- ➙ ፩፻ --- ➙ አሐዱ ምእት
➙ ሰ --- ➙ ፪፻ --- ➙ ክልኤቱ ምእት
ወዘተ እያለ ፊደላቱ ከቁጥር ጋር ዝምድና ያላላቸው መሆኑን ያስረዳል።

*************************

➤ ጥያቄ
፩, በዝርዋን ፊደላት የተጻፉ የግእዝ ቃለትን እያንዳንዳችሁ አምስት አምስት ቃላት ከመዝገበ ቃላት ፈልጋችሁ ጻፉ።
ምሳሌ፦
➙ ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ።
➙ ኲነኔ ➙ ፍርድ
➙ ኊልቍ ➙ ቁጥር
➙ ለሐኰ ➙ ሠራ/ፈጠረ
➙ መኳንንት ➙ ወዘተ
፪, በ ሞክሸ ፊደላትና በዝርዋን ፊደላት ያለውን አንድነትና ልዩነት ጻፉ።።
፫, ስለነዚህ ፊደላት በሰፊው በማንበብ ያላችሁን ማነኛውንም ጥያቄ ጠይቁ።

****************************

፩. ፱ ክፍላተ ዘመን ወጊዜ ፣ መስፈርታት ወአምጣናት

➙ ቀመር = ዘይትኌለቊ በዓመት
➙ ዓመት = ሠለስቱ ምእት ስሳ ወኀምስቱ ዕለታት
➙ ወርኅ = ሠላሳ ዕለታት
➙ ሰንበት= ሰብዐቱ ዕለታት
➙ ዕለት = እሥራ ወአርባዕቱ ሰዓት
➙ ሰዓት = ስሳ ደቃቅ
➙ ደቂቃ = ስሳ ካልኢት
➙ ካልኢት = አሐቲ ቅጽበት

፩. ፲ ክፍላተ ዓመት ወከዋክብቲሆን

➙ መፀው = እም አመ እሥራ ወሰዱሱ ለመስከረም እስከ አመ እሥራ ወኀሙሱ ለታኅሣሥ

➙ ሐጋይ = አም አመ እሥራ ወሰዱሱ ለታኅሣሥ እስከ አመ እሥራ ወኀሙሱ ለመጋቢት

➙ ጸደይ = እም አመ እሥራ ወሰዱሱ ለመጋቢት እስከ አመ እሥራ ወኀሙሱ ለሠኔ

➙ ክረምት = እም አመ እሥራ ወሰዱሱ ለሠኔ እስከ አመ እሥራ ወኀሙሱ ለመስከረም

❖ የመፀው ኮከብ ምልክኤል
❖ የሐጋይ ኮከብ ሕልመልሜሌክ
❖ የጸደይ ኮከብ ሚስኤል
❖ የክረምት ኮከብ ናርኤል ይባላሉ።

፩. ፲፩ ክፍላተ ስምንቱ መአዝናት

➤ አርባዕቱ ዐቢያን
➙ ምሥራቅ
➙ ምዕራብ
➙ ሰሜን
➙ ደቡብ

➤ አርባዕቱ ንዑሳን
➙ መስዕ
➙ አዜብ
➙ ባሕር
➙ ሌብ

፩. ፲፪ ኀምስቱ ክፍላተ ዓለም
❖ አፍሪቃ
❖ እስያ
❖ አውሮፓ
❖ ዖሲያንያ
❖ አሜሪቃ

፩. ፲፫ አስማተ ኀምስቱ ሕዋሳት ወግብራቲሆን

➤ ፭ቱ ሕዋሳት --- ➤ ግብሮን ➤ ትርጉም
➙ ዐይን ---- ➙ ርእይ ---- ➙ ማየት
➙ እዝን ---- ➙ ሰሚዕ ---- ➙ መስማት
➙ አንፍ ---- ➙ አጼንዎ ---- ➙ ማሽተት
➙ አፍ ---- ➙ ጥዒም ---- ➙ መቅመስ
➙ እድ ---- ➙ ገሲስ ---- ➙ መዳሰስ

********** ➤ ጥያቄ ****************

➤በአምስቱ ሕዋሳት የተጻፉ ዐረፍተ ነገሮችን ከመጻሕፍት በመፈለግ ለያንዳንዳቸው ምሳሌ ጻፉ።
ከተቻለ ምዕራፍና ቁጥር

ምሳሌ፦ዐይን
፩ ዐይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ።
(የነፍስ ሁሉ ዐይን አንተን ይታመናል)።

፪ ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ።
(ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ)

፫ አንፍ ቦሙ ወኢያጼንው)።
(አፍንጫ አላቸው ግን አያሸቱም)።

፬ አፉሁ ለጻድቅ ይትሜሀር ጥበበ።
(የጻድቅ አንደበቱ ጥበብን ያወራል ወይም ይማራል)።

፭ ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ።
(እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ)።

***********************************


፩. ፲፬ አስማተ ሰብዐቱ ከዋክብት ዐበይት እለ ይትቀበሉ ብርሃነ እምነ ፀሐይ

፩, አጣርድ ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፪, ዝሑራ ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፫, መሪኅ ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፬, መሽተራ ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፭, ዙሐል ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፮, ኡራኑስ ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ
፯, ነይጡን ➙ ይትቀበል ብርሃነ እምነ ፀሐይ

፩. ፲፭ አስማተ ዐሠርቱ ወክልኤቱ አውራኅ ወከዋክብቲሆን

➤ ወርኅ -------- ➤ ኮከብ ------- ➤ትርጉም
፩, መስከረም ---- ➙ ሚዛን ------- ➙ በቁሙ
፪, ጥቅምት ----- ➙ አቅራብ ------ ➙ ጊንጥ
፫, ኅዳር ------- ➙ ቀውስ ------- ➙ ቀስተኛ
፬, ታኅሣሥ ------ ➙ ጀዲ ------- ➙ ጠቦት
፭, ጥር -------- ➙ ደለው ------ ➙ መቅጃ
፮, የካቲት ------- ➙ ሑት ------- ➙ ዓሣ
፯, መጋቢት------- ➙ ሐመል ------ ➙ አውራበግ
፰, ሚያዝያ ------ ➙ ተውር ------ ➙ በሬ
፱, ግንቦት ------- ➙ ገውዝ ------ ➙ ጥንድ
፲, ሠኔ -------- ➙ ሸርጣን ------- ➙ ጉርምጥ
፲፩, ሐምሌ ------ ➙ አሰድ ------- ➙ አንበሳ
፲፪, ነሐሴ ------- ➙ ሰንቡላ ------- ➙ ባለሽቱ


**************************************

************* ➤ ምልማድ ፩ **************

❖ ኅረይ አሐደ ፊደለ እንተ ነሥአ ርቱዐ አውሥኦተ እንዘ ታነብብ/ቢ እምታሕት ዘሀለዉ ተስእዕሎታተ።

፩, እምዘይተልዉ አሐዱ ዘይትኌለቍ በዐመት ውእቱ

ሀ, ሰንበት ለ, ወርኅ ሐ, ዕለት መ, ቀመር


፪, ዕለት ብሂል ___ ብሂል ውእቱ።

ሀ, ካልኢት ለ, ሰዓት ሐ, ፳ወ፬ቱ ሰዓት መ, ወርኅ


፫, አሐቲ ቅጽበት ብሂል __ብሂል ውእቱ

ሀ, ስሳ ካልኢት ለ, ደቃቅ ሐ, ዕለት መ, ካልኢት


፬, ከሚከተሉት አንዱ በትክክል የተዛመደው የቱ ነው?

ሀ, መፀው ➙ ሚስኤል
ለ, ሐጋይ ➙ ምልክኤል
ሐ, ክረምት ➙ ናርኤል
መ, ጸደይ ➙ ሕልመልሜሌክ

፭, ግብሩ ለዐይን ____ ውእቱ።

ሀ, ሰሚዕ ለ, ርእይ ሐ, ገሲስ መ, አጼንዎ


➤ ምልማድ ፪

❖ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ

፩ በትክክለኛ አጻጻፍ የተጻፈው ቃል የቱ ነው?

ሀ, መፃሕፍት ለ, መፃህፍት ሐ, መጽሐፍት መ, መጻሕፍት

፪, ከሚከተሉት አንዱ በትክክል አልተጻፈም?

ሀ, ድምፅ ለ, ሕሩይ ሐ, መቅደስ መ, እንግዳዕ

፫ ከመጋቢት እስከ ሠኔ ያለው ወቅት ምን በመባል ይታወቃል

ሀ, መፀው ለ, ሐጋይ ሐ, ጸደይ መ, ክረምት

፬, የመፀው ኮከብ ማን በመባል ይታወቃል?

ሀ, ሚስኤል ለ, ናርኤል ሐ, ምልክኤል መ, ሕልመልሜሌክ

፭, መድሀኒት የሚለው ቃል መጻፍ ያለበት በ_______ፊደል ነው።

ሀ, በሀሌታው ለ, በሐመሩ ሐ, በብዙኃኑ መ, በሃገሩ

፮, ሰምዐኒ በእዝኑ ብሎ ነጸረኒ በ ______ ይላል።

ሀ, በዐይኑ ለ, በእዱ ሐ, በአፉሁ መ, በአንፉ

፯, ከሚከተሉት አንዱ ከግእዝ ፊደል አይካተትም።

ሀ, ኀ ለ, ፓ ሐ, ኸ መ, ጳ

❖ ወደ ግራም ወደቀኝም ብናነባቸው ፊደላቸው የማይለወጥ ሦስት የግእዝ ቃላት ጻፉ።
❖ምሳሌ
➙ ትሑት
➙ ንኩን
፰, _________
፱, _________
፲, _________



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት


፩, መዝገበ ሰዋስው ወግሰ ወመዝገበ ቃላት ፦ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
፪, ፍኖተ ግእዝ ፦ ያሬድ ፈንታ
፫, መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው መርኆ መጻሕፍት ፦ ያሬድ ሽፈራው
፬, ጥንታዊ ግእዝ በዘመናዊ አቀራርብ ፦ ዜና ማርቆስ
፭, የልሳነ ግእዝ መማሪያ መጽሐፍ ፦ መ/ር ኀይለ ኢየሱስ መንግሥት
፮, መርኆ ሰዋስው ፦ መ/ር ዘርዐ ዳዊት

ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com