headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት

✤ ክፍለ ትምህርት ፭ ✤

❖ ማነኛውንም ነገር ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ፊደል።

❖ "ኑ" እና "ሁ" እነዚህ ፊደላት በግስ መድረሻና በስም መድረሻ እየገቡ እንደ ጥያቄ ምልክት ያገለግላሉ። ይህም በአወንታና በአሉታ ሊነገር ይችላል።

ምሳሌ ፦ "ሀ" በአወንታ ሲነገር

❖ ጠያቂ ✤

➤ ተሐውርኑ ዮም ኀበ ጎንደር ? ➙ ዛሬ ወደ ጎንደር ትሄዳለህ ?
➤ ትመጽእኑ እኅትከ እምነ ጎጃም ? ➙ እህትህ ከጎጃም ትመጣለች ?
➤ ሀሎኑ አዶናይ በዝ ሰማይ? ➙ በዚህ ሰማይ አምላክ አለን ?
➤ ሀሎኑ ሰብእ በዝንቱ ቤት ? ➙ በዚህ ቤት ሰው አለ ?
➤ ብከኑ ሰረገላ ለሊከ ? ➙ ለአንተ መኪና አለህ ?
➤ ተመየጥከኑ እምነ ሀገርከ ? ➙ ካገርህ ተመለስክ ?
➤ ብኪኑ ንዋይ ውስተ ባንክ ? ➙ ባንክ ቤት ገንዘብ አለህ ?
➤ ይትዐወቅኑ ረኀብ በዝንቱ ሀገር ? ➙ በዚህ ሀገር ረኀብ አለ ?
➤ ሀሎኑ ዝናም በሀገርክሙ ? ➙ ባገራችሁ ዝናብ አለ ?
➤ የኀልፍኑ ዝንቱ ዘመን ? ➙ ይህ ዘመን ያልፋልን ?
➤ ትበልዕኑ ዓሣ በጾም ? ➙ አሣ በጾሞ ትበላለህን ?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

❖ መላሽ ✤

❖ አኮ ኢተሐውር ዮም። = አይ ዛሬ አትሄድም።
❖ እወ ዮም እመጽእ። = አወ ዛሬ እመጣለሁ።
❖ እወ ሀሎ አዶናይ በዝ ሰማይ። = አወ በዚህ ሰማይ አምላክ አለ።
❖ እወ አልቦ ሰብእ በዝንቱ ቤት። = አወ በዚህ ቤት ሰው አለ።
❖ እወ ብየ ሰረገላ። = አወ መኪና አለኝ።
❖ አኮ ኢተመየጥኩ ዓዲ። = አይ ገና አልተመለስኩም።
❖ አኮ አልብየ ንዋይ ውስተ ባንክ። = አይ ባንክ ውስጥ ብር የለኝም።
❖ እወ ይትዐወቅ። = አወ ይታወቀል።
❖ እወ ሀሎ ዝናም በሀገርነ። = ባገራችን ዝናም አለ።
❖ እወ የኀልፍ። = አወ ያልፋል።
❖ እወ እበልዕ ዓሣ በጾም። = አወ በጾም አሣ እበላለሁ

...........................

➤ የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ አጥኑ(ያዙ)።

➽ ዮም ➙ ዛሬ = today
➽ ተመይጠ ➙ ተመለሰ = return
➽ አኮ ➙ አይደለም = no
➽ ትማልም ➙ ትናንት = yesterday
➽ ንወይ ➙ ገንዘብ = money
➽ ሀሎ ➙ አለ = have

ምሳሌ ፦ "ለ" በአሉታ ሲነገር

❖ ጠያቂ ✤
➤ ኢትመጽእኑ እምከ እምነ ጎንደር ? ➙ እናትህ ከጎንደር አትመጣም ?
➤ ኢተሐውርኑ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ? ➙ ወደ ቤተክርስቲያን አትሄድም ?
➤ አልብከኑ እረፍት ጌሰም ? ➙ ነገ እረፍት የለህም ?
➤ አልቦኑ ትምህርት ዮም ? ➙ ዛሬ ትምህርትየለም ?
➤ አልቦኑ ሰብእ በዝንቱ ቤት ? ➙ በዚህ ቤት ሰው የለም ?
➤ ኢትበልዕኑ ሥጋ ላሕም ? ➙ የላም ሥጋ አትበላም ?
➤ ኢተአምሪኑ ልሳነ ግእዝ ? ➙ የግእዝ ቋንቋ አታውቂምን ?
➤ አልብኪኑ ነውር ? ➙ ነውር አታውቂም ?
➤ ኢታከብርኑ ሰንበተ ? ➙ ሰንበትን አታከብሪም ?
➤ ኢይትዐወቅኑ ሀገርከ ? ➙ ሀገርህ አይታወቅም ?

❖ መላሽ ✣

❖ እወ ኢትመጽእ። = አወ አትመጣም።
❖ አኮ ተሐውር ኩለሄ። = አይ ሁልጊዜ ትሔዳለች።
❖ እወ አልብየ እረፍት። = አወ እረፍት ለኝም።
❖ እወ አልቦ ትምህርት ዮም = አወ ዛሬ ትምርት የለም።
❖ እወ አልቦ ሰብእ በዝንቱ ቤት። = አወ በዚህ ቤት ሰው የለም።
❖ እወ ኢይበልዕ ሥጋ ላሕም። = አወ የላም ሥጋ አልበላም።
❖ እወ ኢየአምር ልሳነ ግእዝ። = አወ ግእዝ ቋንቋ አላውቅም።
❖ አኮ ብየ ነውር። = አይ ነውር አለኝ።
❖ አኮ አከብር ሰንበተ = አይደለም ሰንበትን አከብራለሁ
❖ አኮ ይትዐወቅ ሀገርየ። = አይ አገሬ ይታወቃል።

---------------------------

➤ የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ አጥኑ/ ያዙ

➽ እምነ ➙ ከ = " from "
➽ አልቦ ➙ የለም = " No "
➽ ኢየአምር ➙ አላውቅም = " I do not know"
➽ ኩለሄ ➙ ሁልጊዜ = " always "
➽ ላሕም ➙ ላም = " cow "
➽ ጌሰም ➙ ነገ = " tomorrow "

---------------------------

❖ መልመጃ ፩ ( Exercise 1)

➤ በምድብ "ሀ" ሥር ለተዘረዘሩት ቃላት በምድብ "ለ" ሥር ከተዘረዘሩት ቃላት ጋር በተቃራኒያቸው አዛምዱ።

" ሀ " ........ " ለ "
፩, አኮ ........ ሀ, ኀሊፎ ፥ ኀሊፎ
፪, አልቦ ........ ለ, ሶር
፫, ላሕም ........ ሐ, ውእቱ
፬, ኩለሄ ........ መ, ዘኀለፈ
፭, ዓዲ ........ ሠ, ቦ


❖ መልመጃ ፪ ( Exercise 2)

➤ የሚከተሉትን ጥያቄወች በማንበብ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ / ጭ

፩,______ሀሎ ንጉሠ እሥራኤል ዘተወልደ ?

ሀ, መኑ ለ, ምንት ሐ, አይቴ መ, እስፍንቱ

፪, አልብከ _ እረፍት ኦ እኁየ ?

ሀ, ኑ ለ, ሁ ሐ, "ሀ" ወ "ለ" መ, አልቦ
፫,_____ውእቱ ግብሩ ለዝንቱ ብእሲ ?

ሀ, ማዕዜ ለ, ምንት ሐ, እስፍንት መ, ለምንት

፬,_______ተወለድኪ አንቲ ብእሲት ?

ሀ, ምንት ለ, መኑ, ሐ, አኮ መ, ማዕዜ

፭, አኮ ሔኖክ ፀርየ __ ፍቁርየ።

ሀ, ዳእሙ ለ, ባሕቱ ሐ, አላ መ, ኩሉ ይከውን

፮,___አግመረቶ ድንግል ለክርስቶስ ወ ___ፆረቶ በከርሣ

ሀ, እፎ/እፎ ለ, ምንት/እፎ ሐ, ምንት/ምንት መ, አልቦ



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት



ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com