headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት

❖ ክፍለ ትምህርት ፬ ✣

➤ ምክንያታዊነትን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ቃልት

፩,ለምንት ➙ ለምን ➙ why?
✤ ህየንተ ምንት ➙ ስለምን ➙ about what?
✤ በእንተ ምንት ➙ ስለምን ➙ about what?
✤ በምክንያተምንት ➙ በምንምክንያት?

✣ ጠያቂ ✣

❖ ለምንት ትትሜሀር ልሳነ ግእዝ? ➙ የግእዝ ቋንቋ ለምን ትማራለህ?
❖ ለምንት የሐውር ሰብእ ኀበ ቤተ ክርስቲያን? ➙ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለምን ይሔዳል?
❖ ለምንት መጻእከ/ኪ ዮም? ➙ ዛሬ ለምንመጣህ/ሽ?
❖ ለምንት ሖርከ/ኪ ኀበ ጎንደር? ➙ ወደ ጎንደር ለምን ሔድክ/ሽ?
❖ ለምንት ይዜኀር ባዕል? ➙ ባለፀጋ ለምን ይኮራል?
❖ ለምንት ተፈጥረ ሰብእ? ➙ ሰው ለምን ተፈጠረ?
❖ በይነ ምንት ተኀዝን/ኒ? ➙ ስለምን ታዝናለህ/ኛለሽ?
❖ ህየንተ ምንት ተወልደ ክርስቶስ? ➙ ክርስቶስ ስለምን ተወለደ?
❖ በምክንያተ ምንት በከዩ ሕዝብ? ➙ ሕዝቦች ስለምን ምክንያት አለቀሱ?

✣ መላሽ ✣

➤ ለአንብቦተ መጻሕፍት እትሜሀር። ➙ መጽሐፍ ለማንብ እማራለሁ።
➤ ለገቢረ ጸሎት የሐውር። ➙ ጸሎት ለማድረግ ይሔዳል።
➤ ለነጽሮተ ሕንጻ ዘፋሲለደስ። ➙ የፋሲለደስን ሕንጻ ለማየት።
➤ ለተምህሮ ግእዝ መጻእኩ። ➙ ግእዝ ለመማር መጣሁ።
➤ በእንተ በዝኀ ሐብቱ ይዜኀር። ➙ ሐብቱ ስለበዛ ይኮራል።
➤ ለሰብሖተ ፈጣሪ ተፈጥረ ሰብእ። ➙ ሰው ፈጣሪን ለማመስገን ተፈጠረ።
➤ በእንተ ሀገርየ አኀዝን። ➙ ስለሀገሬ አዝናለሁ።
➤ ህየንተ ሰብእ ተወልደ ክርስቶስ። ➙ ክርስቶስ ስለሰው ተወለደ።
➤ በምክንያተ ሀገሮሙ በከዩ። ➙ ስለሀገራቸው ምክንያት አለቀሱ።

።።።።።።።።።።።።።።። ።።።። ።።። ።።

❖ የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ ያዙ/አጥኑ ✣

➽ ህየንተ/በእንተ ➙ ስለ --- ➽ ሰብእ ➙ ሰው
➽ ተዝኅረ ➙ ኮራ ------- ➽ ይዜኀር ➙ ይኮራል
➽ በከየ ➙ አለቀሰ ------- ➽ ባዕል ➙ ባለፀጋ
➽ በዝኀ ➙ በዛ --------- ➽ ሐነጸ ➙ ሰራ
➽ ገብረ ➙ አደረገ ------- ➽ ሀገሮሙ ➙ አገራቸው
➽ ነጸረ ➙ አየ --------- ➽ ይኔጽር ➙ ያያል
➽ ሰብሐ ➙ አመሰገነ ----- ➽ ይሴብሕ ➙ ያመሰግናል

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

➤ ከሁለት አንድ የሆነ አማራጭን ለመጠየቅ የሚያገለግል
መጠይቃዊ ቃል
፪, ❖ አይ ➙ የቱ/የትኛው ➙ which?
❖ አየ ➙ የቱን/የትኛውን ➙ which?
❖ አያት ➙ የቶቹ/የትኞቹ ➙ which?
❖ አያተ ➙ የቶችን/የትኞቹን ➙ which?


❖ ጠያቂ ✣

❖ አይ ውእቱ ርእስከ/ኪ? ➙ ራስህ/ሽ የትኛው ነው?
❖ አይ ውእቱ የማናይ ዐይንከ/ኪ? ➙ ቀኙ ዐይንህ /ሽ የትኛው ነው?
❖ አይ ይኄይስ እምነ ጎንደር ወ አዲስ አበባ? ➙ ከጎንደርና ከአዲስ አበባ የቱ ይሻላል?
❖ አይ የዐቢ እምነ ዐባይ ወ ተከዜ? ➙ ከዐባይና ከተከዜ የቱ ይበልጣል?
❖ አይ ውእቱ ቤትከ/ኪ ➙ ቤትህ/ሽ የትኛው ነው?
❖ አይ ልሳን ዘይትናገር ዘንተ ነገረ? ➙ ይህንን ነገር የሚናገር የትኛው አንደበት ነው?
❖ አየ ትጸልእ ወአየ ታፈቅር እምነስቴ ወ መብልዕ? ➙ ከመብልና ከመጠጥ የትኛውን ትጠላለህ የትኛውንስ ትወዳለህ?
❖ አያት ውእቶሙ አብያጺከ? ➙ ጓደኞችህ የትኞቹ ናቸው?
❖ አያት ወእቶሙ አዕይንቲከ? ➙ ዐይኖችህ የትኞቹ ናቸው?
❖ አያት ውእቶሙ አእጋሪከ? ➙ እግሮችህ የትኞቹ ናቸው?
❖ በአይ ዘመን ይመጽእ ክርስቶስ? ➙ ክርስቶስ በየትኛው ዘመን ይመጣል?
❖ በአይ ዕለት ተሰቅለ ክርስቶስ? ➙ ክርስቶስ በየትኛው ቀንተሰቀለ?
❖ በአይ ዕለት ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን? ➙ ክርስቶስ በየትኛው ቀን ከሙታን መካከል ተነሣ?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

❖ መላሽ ✣

➤ ዝንቱ ውእቱ ርእስየ። ➙ ራሴ ይህ ነው።
➤ ዝንቱ ውእቱ የማናይ ዐይንየ። ➙ ቀኙ ዐይኔ ይህ ነው።
➤ አዲስ አበባ ይኄይስ። ➙ አዲስ አበባ ይሻላል።
➤ ዐባይ የዐቢ እምነ ተከዜ።➙ ከተከዜ ዐባይ ይበልጣል።
➤ ዝንቱ ውእቱ ቤትየ። ➙ ቤቴ ይህ ነው።
➤ ዝንቱ ልሳን ይትናገር ዘንተ ነገረ። ➙ ይህን ነገር ይህኛው አንደበት ይናገራል።
➤ አነ አጸልዕ ስቴ ወባሕቱ አፈቅር መብልዐ። ➙ መጠጥ እጠላለሁ ነገር ግን መብል እወዳለሁ።
➤ እሉ ውእቶሙ አብያጽየ። ➙ እነዚህ ጓደኞቼ ናቸው።
➤ እሉ ውእቶሙ አዕይንትየ። ➙ እነዚህ ዐይኖቼ ናቸው።
➤ እሉ ውእቶሙ አእጋርየ። ➙ እነዚህ እግሮቼ ናቸው።
➤ በማእከላዊ ዘመን ይመጽእ ክርስቶስ። ➙ ክርስቶስ በመካከለኛው ዘመን ይመጣል።
➤ በዕለተ ዐርብ ተሰቅለ ክርስቶስ። ➙ ክርስቶስ ዐርብ ቀን ተሰቀለ።
➤ በዕለተ እሑድ ተንሥአ ክርስቶስ። ➙ ክርስቶስ እሑድ ቀን ተነሣ።

።።።።። ።።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።

➨ የዕለቱ ዋና ዋና ቃላት ✤

❖ ጸልአ ➙ ጠላ -------- ❖ ልሳን ➙ አንደበት
❖ አፍቀረ ➙ ወደደ ------ ❖ ማእከላዊ ➙ መካከለኛ
❖ ተንሥአ ➙ ተነሣ ------ ❖ አእጋር ➙ እግሮች
❖ የማን ➙ ቀኝ -------- ❖ የዐቢ ➙ ይበልጣል
❖ እሉ ➙ እነዚህ ------- ❖ ስቴ ➙ መጠጥ
❖ ውእቶሙ ➙ ናቸው ---- ❖ መብልዕ ➙ መብል


✤ የክፍለ ትምህርት ፬ መልመጃ

➤ የሚከተሉትን ቃላት በተስማሚው ቦታ በማስገባት ባዶ ቦታውን አሟሉ።

አንድ ቃል ሁለት ቦታ ሊገባ ይችላል።

❖ ማዕዜ --------- ❖ አይቴ
❖ መኑ ---------- ❖ እፎ
❖ ምንት --------- ❖ እለመኑ
❖ እስፍንቱ -------- ❖ እስፍንተ
❖ እስከ ማእዜኑ ---- ❖ ለምንት

፩,______ አኀው ሀለውከ ኦ እኁየ?
፪,______ ይከውነኒ ዝንቱ ነገር እንዘ ኢየአምር ብእሴ?
፫,______ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ?
፬,______ ይትበሀል ስመ ዚአከ/ኪ?
፭,______ አነብር ኀዘነ ውስተ ልብየ ይቤ ዳዊት በመዝሙሩ።
፮,______ ነገር ይኄይሰነ ኦ አኀውየ?
፯,______ ሖሩ ዮም ኀበ አሜሪካ?
፰,______ ተወልደት ማርያም ቅድስት?
፱,______ ውእቱ መካነ ህላዌከ/ኪ?
፲,______ ትትሜሀሩ ልሳነ ግእዝ?



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት



ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com