headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት


❖ ክፍለ ትምህርት ፪ ✤

➤ ነገሮችን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ቃል

፫, ምንት ➙ ምን --- what....?
ምንት ምንት ➙ ምን ምን --- what what....?
ምንተ ➙ ምንን --- at what.....?

ምሳሌ ፦

* ምንት ውእቱ ግብርከ/ኪ ➙ ሥራህ ምንድን ነው?
* ምንት ተመሀርከ/ኪ ዮም ➙ ዛሬ ምን ተማርክ/ሽ?
* ምንት በላዕከ/ኪ ዮም ➙ ዛሬ ምን በላህ/ሽ?
* ምንት ሰተይከ/ኪ ትማልም ➙ ትናንት ምን ጠጣህ/ሽ?
* ምንት ይኄይሰነ ➙ ምን ይሻለናል?
* ምንት ምንት ትጼሊ በበዕለቱ ➙ በየቀኑ ምን ትጸልያለህ?
* ምንተ ኀሠሥከ/ኪ ➙ ምንን ፈለክ/ሽ?
* ምንተ ታፈቅር/ሪ ➙ ምንን ትወጃለሽ?
* ምንተ ትጸልዕ/ዒ ➙ ምንን ትጠላለህ/ለሽ?
* ምንተ ትገብሩ ዝየ ➙ እዚህ ምን ትሠራላችሁ?
* ምንተ ንገብር ዝየ ➙ እዚህ ምን እንሠራለን?
* ምንተ ትገብር/ሪ ዝየ➙ እዚህ ምን ትሠራለህ/ሽ?

❖ መልስ ❖

✤ ሐኪም ውእቱ ግብርየ። ➙ ሥራየ ሐኪም ነው።
✤ ልሳነ ግእዝ ተመሀርኩ ዮም። ➙ ዛሬ ግእዝ ተማርኩ።
✤ ኅብስተ መና በላዕኩ ዮም።➙ መና የሆነ እንጀራ ዛሬ በላሁ።
✤ ትማልም ሰተይኩ ወይነ። ➙ ትናንት ጠላ ጠጣሁ።
✤ ይኄይሰነ ንትሜሀር ትምህርተ። ➙ ትምርት ብንማር ይሻለናል።
✤ ጸሎተ ማርያም ወውዳሴ ማርያም ጸሎተ ማርያምና እጼሊ
በበዕለቱ። ➙ ውዳሴ ማርያም በየቀኑ እጸልያለሁ።
✤ አነ ኀሥኩ ምግበ። ➙ እኔ ምግብ እፈልጋለሁ።
✤ አነ አፈቅር ተውኔተ ኳሄላ። ➙ ኳስ ጨዋታ እወዳለሁ።
✤ አነ እጸልዕ ነገረ። ➙ እኔ ነገርን እጠላለሁ።
✤ ንሕነ ንገብር ግብረ እድ። ➙ እኛ የእጅ ሥራን እንሠራለን።
✤ ዝየ ንግበር ማኅደረ። ➙ እዚህ ቤትን እንሥራ።
✤ አነ እገብር ግብረ ቤትየ።➙እኔ የቤት ሥራየን እሠራለሁ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

➤ አንድ ነገር ምን ያህል መሆኑን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት
መጠይቃዊ ቃላት

፬, እስፍንቱ ... ስንት.. How much....?
በእስፍንቱ ... በስንት. in how much...?
እስፍንተ ... ስንትን. .....?

ምሳሌ፦

* እስፍንቱ ውእቱ ዕድሜከ/ኪ ➙ ዕድሜህ ስንት ነው?
* እስፍንቱ አኀው ሀለውከ/ኪ ➙ ስንት ወንድሞች አሉህ?
* እስፍንቱ አኀት ሀለውከ/ኪ ➙ ስንት እኅቶች አሉህ/ሽ?
* እስፍንቱ ዐመት ተመሀርከ/ኪ ➙ ስንት ዐመት ተማርክ/ሽ?
* እስፍንቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ ➙ አሁን ስንት ሰዓት ነው?
* እስፍንቱ ዉሉድ ሀለውከ/ኪ ➙ ስንት ልጆች አሉህ/ሽ?
* በእስፍንቱ ሰዓት ትመጽእ/ኢ ➙ በስንት ሰዓት ትመጣለህ?
* በእስፍንቱ ሰዓት ተሐውር/ሪ ➙ በስንት ሰዓት ትሔዳለህ?
* እስፍንተ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ ➙ ክርስቶስ ስንት
ሐዋርያትን መረጠ?

❖ መልስ ✣

➤ እሥራ ወስድስቱ ውእቱ ዕድሜየ። ➙ ዕድሜየ
ሃያ ስድስት ነው።
➤ ሠለስቱ አኀው ሀለውኒ። ➙ ሦስትወንድሞች አሉኝ።
➤ ክልኤቱ አኀት ሀለውኒ። ➙ ኹለት ወንድምች አሉኝ።
➤ ስድስቱ ዓመት ተመሀርከ። ➙ ስድስት ዐመትተማርኩ።
➤ ሠለስቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ። ➙ አሁን ሦስት ሰዓት ነው።
➤ አርባዕቱ ውሉድ ሀለውኒ። ➙ አራት ልጆች አሉኝ።
➤ በክልዔቱ ሰዓት እመጽእ። ➙ በኹለት ሰዓት አመጣለሁ።
➤ በስድስቱ ሰዓት አሐውር። ➙ በስድስት ሰዓት እሔዳለሁ።
➤ ዐሠርተ ወክልኤተ ኀረየ ክርስቶስ ። ➙ ፲፪ ሐዋርያትን
ክርስቶስ መረጠ።

❖ የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ አጥኑ(ያዙ) ✣

* ገብረ ➙ ሠራ ------ ይገብር ➨ ይሠራል
* መሀረ ➙ አስተማረ --- ይሜህረ ➨ ያስተምራል
* በልዐ ➙ በላ ------ ይበልዕ ➨ ይበላል
* ሰትየ ➙ ጠጣ ----- ይሰቲ ➨ ይጠጣል
* ኀየሰ ➙ ተሻለ ------ ይኄይስ ➨ ይሻላል
* ጸለየ ➙ ለመነ ------ ይጼሊ ➨ ይለምናል
* ኀሠሠ ➙ ፈለገ ----- የኀሥሥ ➨ ይፈልጋል
* ኀረየ ➙ መረጠ ----- የኀሪ ➨ ይመርጣል
* አፍቀረ ➙ወደደ ------ ያፈቅር ➨ ይወዳል
* ሀለወ ➙ ኖረ ------ ይሄሉ ➨ ይኖራል
* ወለደ ➙ ወለደ ----- ይወልድ ➨ ይወልዳል
* መጽአ ➙ መጣ ----- ይመጽእ ➨ ይመጣል
* ሖረ ➙ ሔደ ----- የሐውር ➨ ይሔዳል

✣ መልመጃ ፩

❖ በምድብ "ሀ" ሥር ለቀረቡት ቃላት በምድብ "ለ"
ሥር ከተዘረዘሩት ቃላት ከተመሳሳዮቻቸው ጋር አዛምዱ።

----- " ሀ " ...... " ለ"
----፩, ሖረ ...... ሀ ሐነጸ
----፪, ገብረ ...... ለ ቦ
----፫, ሀለወ ...... ሐ ነገደ
----፬, መጽአ ...... መ ሠምረ
----፭, አፍቀረ ...... ሰ ቀርበ


❖ መልመጃ ፪

❖ የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች በማንበብ ትክክለኛ መልስ ያዘውን
ፊደል ምረጥ /ጭ።

፩, _ ውእቱ ዕድሜከ/ኪ

ሀ, መኑ ለ, ምንት ሐ, እስፍንቱ መ, አልቦ

፪, ኦ እኁየ __ ትሴኒ መርዓትከ

ሀ, እስፍንቱ ለ, መኑ ሐ, እፎ መ, ምነተ

፫, ምንት ውእቱ ________ ዝንቱ ነገር

ሀ,ዛቲ ለ, ዝንቱ ሐ, እሉ መ, እንታክቲ

፬, ምንት ___ ዛቲ ነገር

ሀ, ውእቱ ለ, ውእቶሙ ሐ, ይእቲ መ, ውእቶን

፭, ለእመ አልብነ ግብር ምንተ ንበልዕ ወ ____ ንለብስ

ሀ, ምንት ለ, መኑ ሐ, እስፍንቱ መ, ምንተ

፮, ንሕነ እርድእት __ ግብረ ቤትነ በጊዜሁ።

ሀ, እግበር ለ, ትግበር ሐ, ይግበር መ, ንግበር

፯, መኑ __ ስምከ ኦ እኁየ

ሀ, ይተበሀል ለ, ትትበሀል ሐ, ንትበሀል መ, እትበሀል

፰, _ መጻእኪ ኀቤነ ኦ እኅትነ

ሀ, እስፍንቱ ለ, መኑ ሐ, እፎ መ, ምንት

፱ ዳዊት፦ እፎ ውእቱ ሕይወት
አቤል፦ ______________።

ሀ, እግዚአብሔር ይሰባሕ
ለ, ይትባረክ እግዚአብሔር
ሐ ምንተኑመ ኢይብል
መ, ኲሉ ይከውን አውሥኦት

፲, ራሔል፦ምንት ተኀሥሢ ዝየ ርብቃ
ርብቃ፦ አነ _____አብያጽየ።

ሀ, ነኀሥሥ ለ, የኀሥሥ ሐ, አኀሥሥ መ, ተኀሥሥ

።።።።።።።።።። ።።።።።። ።። ።።።።።።።።።።።።

❖ የዕለቱ ዋና ዋና ቃላት ✤

* ዝንቱ ➙ ይህ ...... * ዛቲ ➙ ይች
* ውእቱ ➙ ነው ...... * እንታክቲ ➙ ያች
* ኀሠሠ ➙ ፈለገ ...... * ውእቶሙ ➙ ናቸው
* ኲሉ ➙ ኹሉ ...... * ይእቲ ➙ ናት
* ይከውን ➙ ይሆናል ...... * አርድእት ➙ ተማሪዎች
* እኁየ ➙ ወንድሜ ...... * አብያጽየ ➙ ጓደኞቼ
* ኳሄላ ➙ ኳስ ...... * አልቦ ➙ የለም

።።።።።።።።።። ።።።።።። ።። ።።።።።።።።።።።።



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት



ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com