headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት

❖ ክፍለ ትምህርት ፫ ✣

➤ ጊዜን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ቃል ✤

፭, ማዕዜ ➙ መቼ ➙ when
✤ እስከ ማዕዜኑ ➙ እስከ መቼ ➙ until when
✤ ማዕዜ ማዕዜ ➙ መቼ መቼ ➙

✤ ጠያቂ ✤

ምሳሌ፦

❖ ማዕዜ ተወለድከ/ኪ ➙ መቼ ተወለድክ/ሽ ?
❖ ማዕዜ ተወጥነ ትምህርት ➙ ትምህርት መቼ ተጀመረ ?
❖ ማዕዜ ይኩን ከብካብነ ➙ ሰርጋችን መቼ ይሁን ?
❖ ማዕዜ ንሑር ኀበ ሐዋሳ ➙ ወደ አዋሳ መቼ እንሂድ ?
❖ ማዕዜ ንምጻእ ➙ መቼ እንምጣ ?
❖ ማዕዜ ትመጽእ ➙ መቼ ትመጣለህ ?
❖ ማዕዜ ትመጽእ እኅትከ/ኪ ➙ እኅትህ/ሽ ?
❖ ማዕዜ ማዕዜ ትትሜሀር ልሳነ ግእዝ ➙ የግእዝ ቋንቋ መቼ መቼ ትማራለህ ?
❖ ማዕዜ ማዕዜ ተሐውሩ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ➙ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቼ መቼ ትሔዳላችሁ ?
❖ ማዕዜ ይመጽእ ክርስቶስ ➙ ክርስቶስ መቼ ይመጣል ?
❖ እስከ ማዕዜ ትጸንሕ ዝየ ➙ እዚህ እስከ መቼ ትቆያለህ ?
❖ እስከ ማዕዜ ትመጽእ ➙ እስከ መቼ ትመጣለህ ?
❖ እስከ ማዕዜ ትመጽኢ ➙ እስከ መቼ ትመጫለሽ ?

❖ መላሽ ✤

➤ አነ ተወለድኩ አመ ዕሥራ ወሠለስቱ ለኅዳር። ➙ እኔ ኅዳር ሃያ ሦሥት ቀን ተወለድኩ።
➤ መስከረም ዐሥርቱ ተወጥነ ትምህርት። ➙ መስከረም ዐሥር ትምር ተጀመረ።
➤ በዕለተ እሑድ ይኩን ከብካብነ ➙ እሑድ ቀን ይሑን ሠርጋችን።
➤ ጌሰም ንሑር ኀበ ሐዋሳ። ➙ ወደ አዋሳ ነገ እንሒድ።
➤ ጌሰም ንምጻእ። ➙ ነገ እንምጣ።
➤ ድኅረ ጌሰም እመጽእ። ➙ ከነገ በኋላ እመጣለሁ።
➤ ዮም ትመጽእ እኅትየ። ➙ እኅቴ ዛሬ ትመጣለች።
➤ በዕለተ ረቡዕ ወዓርብ እትሜሀር ልሳነ ግእዝ። ➙ ረቡዕ እና ዐርብ ግእዝ ቋነቋ እንማራለን።
➤ በእለተ ሰንበት ነሐውር ኀበ ቤተ ክርስቲያን። ➙ በሰንበት ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄዳለን።
➤ አመ ፍጻሜሀ ለዓለም ይመጽእ ክርስቶስ። ➙ በዓለም መጨረሻ ጊዜ ክርስቶስ ይመጣል።
➤ እስከ እፌጽም ትምህርትየ እጸንሕ ዝየ። ➙ ትምርቴን እስከምጨርስ እዚህ እቆያለሁ።
➤ እስከነ ረቡዕ እመጽእ። ➙ እስከረቡዕ ድረስ እመጣለሁ።
➤ በዘይመጽእ ዓመት እመጽእ። ➙ በሚመጣው ዐመት አመጣለሁ።

❖ የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ አጥኑ ✣

❖ ወለደ ➙ ወለደ ...... ❖ ይወልድ ➙ ይወልዳል
❖ ወጠነ ➙ ጀመረ ...... ❖ ይዌጥን ➙ ይጀምራል
❖ ጸንሐ ➙ ቆየ ....... ❖ ይጸንሕ ➙ ይቆያል
❖ ፈጸመ ➙ ጨረሰ ...... ❖ ይፌጽም ➙ ይጨርሳል
❖ መጽአ ➙ መጣ ...... ❖ ይመጽእ ➙ ይመጣል
❖ ኮነ ➙ ኾነ ...... ❖ ይከውን ➙ ይሆናል

➤ ቦታን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃውያን ቃላት

፮, አይቴ ➙ የት/ወዴት ➙ Where
✤ ኀበ አይቴ ➙ ወደ የት ➙ To where
✤ እም አይቴ ➙ ከየት ➙ From where

ምሳሌ፦
❖ ጠያቂ ✤

❖ አይቴ ውእቱ ቤትከ/ኪ ➙ ቤትህ/ሽ የት ነው?
❖ አይቴ ይትረከብ ቤትከ/ኪ ➙ ቤትህ/ሽ የት ይገኛል?
❖ አይቴ ውእቱ ብሔራ ለጥብ ➙ የጥብ ሀገሯ የት ነው?
❖ አይቴ ወዐልከ/ኪ ዮም ➙ ዛሬ የት ዋልክ/ሽ?
❖ አይቴ ትውዕል ጌሰም ➙ ነገ የት ትውላለህ?
❖ አይቴ ትውዕሊ ጌሰም ➙ ነገ የት ትውያለሽ?
❖ አይቴ ንትራከብ ➙ የት እንገናኝ?
❖ አይቴ ተመሀርከ ትምህርተከ➙ትምርትህን የት ተማርክ?
❖ አይቴ ፈጸምኪ ትምህርተኪ➙ትምርትሽን የት ጨረስሽ?
❖ ኀበ አይቴ ተሐውር ➙ ወደ የት ትሄዳለህ?
❖ ኀበ አይቴ ተሐውሪ ➙ ወደ የት ትሄጃለሽ?
❖ ኀበ አይቴ ትረውጽ ➙ ወዴት ትሮጣለህ?
❖ ኀበ አይቴ ትረውጺ ➙ ወዴት ትሮጫለሽ?
❖ ኀበ አይቴ ንሑር ➙ ወዴት እንሂድ?
❖ አይቴ ተወለድከ/ኪ ➙ የት ተወለድክ/ሽ?
❖ አይቴ ውእቱ መካነ ግብርከ/ኪ? ➙ የሥራ ቦታህሽ የት ነው?
❖ አይቴ ውእቱ መካነ ህላዌከ/ሽ? ➙ መኖሪያ ቦታህ/ሽ የት ነው?
❖ እም አይቴ መጻእከ/ኪ ➙ ከየት መጣህ/ሽ?
❖ እም አይቴ ትነብር ➙ ከየት ትቀመጣለህ?
❖ እም አይቴ ትነብሪ ➙ ከየት ትቀመጫለሽ?

❖ መላሽ ✤

➤ ሳሪስ ውእቱ ቤትየ። ➙ ቤቴ ሳሪስ ነው።
➤ ኮተቤ ይትረከብ ቤትየ። ➙ ቤቴ ኮተቤ ይገኛል።
➤ ኢትዮጵያ ውእቱ ብሔራ ለጥበብ። ➙ የጥበብ ሀገሯ ኢትዮጵያ ነው።
➤ ዮም ወዐልኩ ፒያሳ። ➙ ዛሬ ፒያሳ ዋልኩ።
➤ ጌሰም እውዕል አራት ኪሎ። ➙ ነገ አራት ኪሎ እውላለሁ።
➤ ጌሰም እውዕል ውስተ ቤትየ። ➙ ነገ ቤቴ ውስጥ እውላለሁ
➤ መርካቶ ንትራከብ። ➙ መርካቶ እንገናኝ።
➤ አዲስ አበባ መካነ አእምሮ ተመሀርኩ። ➙ አዲስ አበባ ዩንበርስቲ ተማርኩ።
➤ አዲስ አበባ መካነ አእምሮ ፈጸምኩ። ➙ አዲስ አበባ ዩንበርስቲ ጨረስኩ።
➤ ኀበ ቤትየ አሐውር።➙ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ።
➤ ኀበ ቤተ ክርስቲያን አሐውር። ➙ ወደ ቤተ ክርስቲያን እሄዳለሁ።
➤ ንሑር ኀበ ቤተ ትምህርት። ➙ ወደ ትምህርት ቤት እንሂድ።
➤ አዲስ አበባ ተወለድኩ። ➙ አዲስ አበባ ተወለድኩ።
➤ ቦሌ ውእቱ መካነ ግብርየ። ➙ የሥራ ቦታየ ቦሌ ነው።
➤ ፈረንሳይ ውእቱ መካነ ህላዌየ። ➙ መኖሪያ ቦታየ ፈረንሳይ ነው።
➤ መጻእኩ እምነ ግብርየ። ➙ ከሥራ ቦታየ መጣሁ።
➤ አነ እነብር ዝየ። ➙ እኔ እዚህ እቀመጣለሁ።
➤ አነ እነብር ላዕለ መንበር። ➙ እኔ በወንበር ላይ እቀመጣለሁ።

❖ መልመጃ ✤

በምድብ "ሀ" ሥር ለተዘረዘሩት ቃላት በምድብ "ለ" ሥር ከተዘረዘሩት ቃላት ከተቃራኒያቸው ጋር አዛምዱ።

ምድብ "ሀ" ምድብ "ለ"
-----፩, ዮም ...... ሀ, ተንሥአ
-----፪, ረከበ ...... ለ, ቅድመ
-----፫, ወጠነ ...... ሐ, ቅሩብ
-----፬,ላዕል ...... መ, ትማልም
-----፭, ነበረ ...... ረ, ኀጥአ
-----፮, ድኅረ ...... ሰ, ፈጸመ
-----፯, ርሑቅ ...... ቀ, ታሕት

❖የሚከተሉትን ጥያቄወች በማንበብ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ/ጭ

፩, __ ተወልደት ማርያም?
ሀ, መኑ ለ, ምንት ሐ, ማዕዜ መ, እስፍንቱ
፪, __ ብሔራ ለጥበብ?
ሀ, አይቴ ለ, እስፍንቱ ሐ, መኑ መ, ለምንት
፫, __ ሖረት እኅትከ/ኪ?
ሀ, ማዕዜ ለ, አይቴ ሐ, ምንት መ, "ሀ"ወ "ለ"
፬, __ አነብር ኀዘነ ውስተ ልብየ?
ሀ, ማዕዜኑ ለ, እስከማዕዜኑ ሐ, ምንትኑ መ, እፎ
፭, ኀበ አይቴ __ አንቲ ሕጻን?
ሀ, ተሐውር ለ, ተሐውሪ ሐ, አሐውር መ, ነሐውር
፮, አይቴ __ አንተ አብርሃም?
ሀ, ወዐልኪ ለ, ወዐልክሙ ሐ, ወዐልከ መ, ወዐልክን
፯, ገበየሁ፦ ማዕዜ መጻእኪ ሐና?
ሐና፦ ___________።
ሀ,ዮም እመጽእ ለ, ጌሰም መጻእኩ ሐ, ይእዜ መጻእኩ መ, ትማልም እመጽእ
፰, አይቴ__ሐና እምየ?
ሀ, ውእቱ ለ, ይእቲ ሐ, ዛቲ መ,ዝንቱ
፱, ማዕዜ __ አንቲ ወለት?
ሀ, ትመጽእ ለ, ይመጽእ ሐ, ንመጽእ መ,ትመጽኢ
፲, __ ይትረከብ ቤተ ክርስቲያንከ?
ሀ, ምንት ለ, መኑ ሐ, አይቴ መ, እስፍንቱ

➤የዕለቱ ዋና ዋና ቃላት ❖

❖ ዮም ➙ ዛሬ ....... ❖ መካን ➙ ቦታ
❖ ናሁ ➙ አሁን ....... ❖ ከብካብ ➙ ሠርግ
❖ ትማልም ➙ ትናንት ....... ❖ ትፍሥሕት ➙ ደሥታ
❖ ይዕዜ ➙ ዛሬ ....... ❖ ጸንሐ ➙ ቆየ
❖ ኀበ ➙ ወደ ....... ❖ አንከረ ➙ አደነቀ
❖ አይቴ ➙ የት ....... ❖ ምሕረት ➙ ይቅርታ
❖ ማዕዜ ➙ መቼ ....... ❖ ጌሰም ➙ ነገ



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት



ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com