headerphoto

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት የዚህ ሳምንት ክፍለ ትምህርት

************ ቀዳማይ ክፍል ********
ክፍለ ትምህርት ፩

✣ መጠይቃውያን ቃላት

፩, መኑ ➙ ማን ➙ Who?
መነ ➙ ማንን ➙ who?
እለ መኑ ➙እነ ማን ?

✣ጥያቄ❖

ምሳሌ ፦
➤ መኑ ውእቱ ስምከ? ➙ ስምህ ማነው?
➤ መኑ ይትበሀል ስምከ ➙ ስምህማን ይባላል?
➤ መኑ ይትበሀል ስምኪ ➙ ስምሽ ማን ይባላል?
➤ መኑ ወለደከ/ኪ ➙ ማን ወለደህ/ሽ
➤ መኑ ፈጠረከ/ኪ ➙ ማን ፈጠረህ/ሽ
➤ መኑ ይትበሀል አቡከ/ኪ ➙ አባትህ/ሽ ማንይባላል
➤ መኑ ትትበሀል እምከ/ኪ ➙ እናትትህ/ሽ ማን ትባላለች
➤ መኑ መጽአ ናሁ ➙ አሁን ማን መጣ
➤ መኑ ሖረ ናሁ ➙ አሁን ማን ሄደ
➤ መኑ ወእቱ ስምክሙ/ክን ➙ ስማችሁ ማን ነው
➤ እለ መኑ ወእቶሙ እሉ አርድእት ➦ አነዚህ ተማሪዎች
አነ ማን ናቸው
➤ መነ ተኀሥሥ/ሢ ➙ ማንን ትፈልጋለህ/ትፈልጊያለሽ
➤ መነ ታፈቅር/ሪ ➙ ማንን ትወዳለህ/ትወጃለሽ

።።።።።።።። ✤ መልስ ❖።።።።።።።።።።።

➨ ዳዊት ውእቱ ስምየ ። ➙ ስሜ ዳዊት ነው።
➨ ዳዊት ይትበሀል ስምየ።➙ ስሜ ዳዊት ይባል።
➨ ሔዋን ይትበሀል ስምየ። ➙ ስሜ ሔዋን ይባላል።
➨ አቡየ ወእምየ ወለዱኒ። ➙ አባትና እናቴ ወለዱኝ።
➨ እግዚአብሔር ፈጠረኒ።➙ እግዚአብሔር ፈጠረኝ።
➨ ያሬድ ይትበሀል አቡየ።➙ አባቴ ያሬድ ይባላል።
➨ ቅድስት ትትበሀል እምየ።➙ እናቴ ቅድስት ትባላለች።
➨ መምህር መጽአ ናሁ።➙ አሁን መምህር መጣ።
➨ ነቢዩ ሖረ ናሁ። ➙ ነቢዩ አሁን ሄደ።
➨ ደረጀ ወሐብታሙ ውእቱ ስምነ። ➙ ስማችን ደረጀና
ሐብታሙ ነው።
➨ እለ አብርሃም ውእቶሙ። ➙ እነ አብርሃም ናቸው።
➨ አነ አኀሥሥ አቤልሀ። ➙ እኔ አቤልን እፈልጋለሁ።
➨ አነ አፈቅር አስቴርሀ። ➙ አኔ አስቴርን እወዳለሁ።

--------------------------------------

፪, እፎ ➙ እንዴት ➙ How
እፎ ፥ እፎ ➙እንዴት እንዴት ፥ ምንኛ

✤ ጥያቄ ✣

ምሳሌ ፦
➤ እፎ ኀደርክሙ ➙ እንዴት አደራችሁ።
➤ እፎ ወዐልክሙ ➙ እንዴት ዋላችሁ።
➤ እፎ ወዐልከ/ኪ ➙ እንዴት ዋልክ /ሽ።
➤ እፎ ወእቱ ሕይወት ➙ ሕይወት እንዴት ነው።
➤ እፎ ውእቱ ግብር➙ሥራ እንዴት ነው።
➤ እፎ ውእቱ ህላዌከ/ኪ➙ኑሮህ እንዴት ነው።
➤ እፎ እፎ ተዋነይከ ብየ➙እንዴ እንዴት ተጫወትክብኝ
➤ እፎ ይኩን ዝንቱ ነገር➙ይህ ነገ እንዴት ይሁን።

✤ መልስ ❖

➤ ይትባረክእግዚአብሔር ➙ እግዚአብሔር ይመስገን።
➤ ጥቀ ሠናይ ወእቱ ➙ በጣም ጥሩ ነው።
➤ ምንተኑመ ኢይብል ➙ ምን አይልም።
➤ ጸልዮ ኀበ እግዚአብሔር ይኄይሰኒ ➙ ወደ እግዚአብሔር
መጸለይ ይሻለኛል።
➤ ጥቀ ሠናይ ውእቱ ➙ በጣም ጥ ነው።
➤ ይኩን በከመ ፈቀድከ ➙ እንደ ወደድክ ይሁን

።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምልማድ ፩

❖የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትርጉም የሚመሳሰሉትን ከ"ለ"ስር ያሉትን
.........ከ"ሀ"ስር ካሉት ጋር አዛምድ/ጅ

......... "ሀ" ........ " ለ"
----- ፩, ጸለየ ........ ሀ, ፍጹመ
------፪, ቡራኬ ........ ለ, አደመ
------፫, ተውኔት ........ ሐ, ሕይውና
------፬, ምንተኑመ ........ መ, ተንበለ
------፭, ሰቆቃው ........ ሰ, ትረጓሜ
------፮, ጥቀ ........ ረ, ወይሌ
------፯, ዐቃቢ ........ ሠ, ወሚመ
------፰, ሠነየ ........ ቀ, ማኅሌት
------፱, ህላዌ ........ በ, ስባሔ
------፲, ፍካሬ ........ ተ, ኖላዊ

ምልማድ ፪

❖የሚከተሉት ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ/ጭ

__፩, ___ወዐልክሙ አንትሙ አርድእት

ሀ, መኑ ለ, መነ ሐ, እፎ መ, እለመኑ

__፪, መነ ታፈቅሪ ወ___ትጸልዒ አንቲ ብእሲት

ሀ, መኑ ለ, መነ ሐ, እፎ መ, አልቦቱ ሚጠት

__፫,____ወእቶሙ ዘቀደሱ ቅዳሴ ዮም

ሀ, መኑ ለ, እፎ ሐ, ምንተኑ መ, እለመኑ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።



ስለ ግእዝ የተጻፉትንና በግእእዝ የተጻፉ መጻሕፍትን ያንብቡ

ዋቤ መጻሕፍት


፩, መዝገበ ሰዋስው ወግሰ ወመዝገበ ቃላት ፦ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
፪, ፍኖተ ግእዝ ፦ ያሬድ ፈንታ
፫, መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው መርኆ መጻሕፍት ፦ ያሬድ ሽፈራው
፬, ጥንታዊ ግእዝ በዘመናዊ አቀራርብ ፦ ዜና ማርቆስ
፭, የልሳነ ግእዝ መማሪያ መጽሐፍ ፦ መ/ር ኀይለ ኢየሱስ መንግሥት
፮, መርኆ ሰዋስው ፦ መ/ር ዘርዐ ዳዊት

ስለ ግእዝ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሆነውን ግእዝን በመማር ሌሎችም እንዲማሩ ያድርጉ።....

አስተያየት ካለ ይጻፉ



ግእዝን ለመማር እዚህ ይመዝገቡ




አጠቃላይ የትምህርቱ መክሥተ አርእስት


  • ምዕራፍ ፩
    • መግቢያ - ፊደል ወትርጓሜ ፊደላት
      • የፊደል ትርጒም
      • የግእዝ ፊደላት
    • ፩.፩ የዕለት ከዕለት የምንግባባቸው ንግግሮች
      • መጠይቃውያን ቃላት
      • ራስን ማስተዋወቅ
      • ጓደኛን ማስተዋወቅ
      • ስለሰዐት መጠየቅና መመለስ
      • የተለያዩ የስልክ ንግግሮች
    • ፩.፪ ተውላጠ ስም{መራህያን}
      • በተሳቢነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • አመልካች ተውላጠ ስሞች
      • በባለቤትነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • በዘርፍነት የሚገቡ ተውላጠ ስሞች
      • ድርብ ተውላጠ ስሞች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፪
    • ፪.፩ ግስና የግስና ዐይነቶች
      • አርእስተ ግስ
      • አዕማድ ግስ
      • አድራጊ {ገቢር}
      • አስደራጊ
      • አደራራጊ
      • ተደራጊ
      • ተደራራጊ
    • ፪.፪ አንቀጽ { Tense}
      • ኀላፊ አንቀጽ
      • ትንቢት አንቀጽ
      • ዘንድ አንቀጽ
      • ትእዛዝ አንቀጽ
  • ምዕራፍ ፫
    • ፫.፩ ዐሥራው ቀለማት{ፊደላት}
      • ዐመላተ ዐሥራው ቀለማት
      • ዐሥራው በ"ሀ" እና በ"አ"ግስ ጊዜ
      • የዐሥራው ቀለማት ባሕርያት
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፬
    • ፬.፩ ስምና የስም ዐይነቶች
      • የስም ብዜት
      • ተመሣሣይና ተቃራኒ ቃላት
      • የቤት እንስሳ ስሞች
      • የዱር እንስሳ ስሞች
      • የሰውነት ክፍል ስሞች
      • የቁሳቁስ ስሞች
      • የዕፀዋት ስሞች
      • የአዝርዕት ስሞች
      • የቅመማ ቅመም ስሞች
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፭
    • ፭.፩ ቅጽል {Adjective}
    • ፭.፪ የቅጽል ዐይነቶች
      • ውስጠዘ ቅጽላት
      • ሣልስ ቅጽል
      • ሳድስ ቅጽል
      • ስማዊ ቅጽል
      • መጠን ገላጭ ቅጽል
      • ቁጥር ገላጭ ቅጽል
      • መተርጉም ቅጽል
      • መድበል ቅጽል
      • መልመጃዎች
    • ፭.፫ መካነ ቅጽላት
  • ምዕራፍ ፮
    • ፮.፩ ተውሳከ ግስና ዐይነቶቹ
      • ጊዜ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • መጠን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ኹኔታ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ቦታን ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ድግግሞሽ ገላጭ ተውሳከ ግስ
      • ምክንያታዊ ተውሳከ ግስ
      • መልጃዎች
    • ፮.፪ ተሳቢ {Adjective}
      • የተሳቢ ሕጎች
      • ገቢር ዐረፍተ ነገር
      • ተገብሮ ዐረፍተ ነገር
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፯
    • ፯.፩ አገባቦች
      • ዐቢይ አገባብ
      • ንዑስ አገባብ
      • ደቂቅ አገባብ
      • አሉታዊ መስተዋድድ
      • አወንታዊ መስተዋድድ
      • መልመጃወች
  • ምዕራፍ ፰
    • ፰.፩ ሥርዓተ ንባብ ሕጎች
      • የተነሽ ንባብ ሕጎች
      • የተጣይ ንባብ ሕጎች
      • የወዳቂ ንባብ ሕጎች
      • የሰያፍ ንባብ ሕጎቸ
      • የሌሎች ንባባት ሕጎች
      • መልመጃዎች
  • ምዕራፍ ፱
    • ፱.፩ ቅኔና የቅኔ ዐይነቶች
      • የቅኔ ዜማ ልክ
      • የቅኔ ሙያ
      • የቅኔ ትርጉም
      • የቅኔ አመጣጥ
      • መልመጃዎች
This website is designed by Dereje G - Contact address Mob. +251912613120 / Email - webadmin@lisanegeez.com / deereey@yahoo.com